text
stringlengths
707
989
### Text: አቡ ባክር አልባግዳዲየአይ ኤስ ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ ድምጹን ካጠፋ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክቱን አስተላልፏል። ቡድኑ ለተነጠቃቸው ይዞታዎችም የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ዝቷል።በአውሮፓውያኑ 2014 ሞሱል በተባለችው የሶሪያ ከተማ ውስጥ ሆኖ በሶሪያና ኢራቅ ላይ እስላማዊ ካሊፌት መመስረቱን ካወጀ በኋላ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቀርቶ ነበር።በተንቀሳቃሽ ምስሉ በቅርቡ በባጉዝ ያጋጠማቸውን ሽንፈት ያመነ ሲሆን መልዕክቱ መቼ እንደተቀረጸ ...
### Text: ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል በቀን 28022012ዓም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል ለሚዲያ አካላት የተሰጠ መግለጫትናንት በ270220...
### Text: አፍሪካ ሕብረት እንዲገኝ ጥሪ አልደረሰንም ኤባ ካሎንዶአዲሱ የቡድን 20 የበለጸጉ ሀገራት ዓባል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘ ገልጿል።ነገ ዓርብ እና ቅዳሜ በኒው ደሊ የሚካሄደውን ጉባኤ ያዘጋጀችው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ አፍሪካዊው ድርጅት ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገው ነበር።የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ቃል አቀባይ የሆኑት ኤባ ካሎንዶ፣ ኅብረቱ በጉባኤው ላይ እንዲገ...
### Text: የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተዳደር እና የሠራተኛ ማህበር እሰጥ አገባበኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ውስጥ ከሚገኙት የሠራተኛ ማህበራት አንዱ ከአየር መንገዱ አስተዳደር ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል።በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ሁለት የሠራተኛ ማህበራት ይገኛሉ። እኚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ይሰኛሉ።ቀዳማዊ የምትለዋን ቃል በውስጡ የያዘው የሠራተኛ ማህበር የተመሰረ...
### Text: አሁንም በአካባቢው ስጋት በመኖሩ የመከላከያ ኃይል ወደ አካባቢው እንዲላክልን ጠይቀናል አበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ደስታ ለማአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በኒሯቅ ከተማ ትናንት ታጣቂዎች ጥቃት ከፍተው በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ለማ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቀዋል።አሁንም በአካባቢው ስጋት በመኖሩ የመከላከያ ኃይል ወደ አካባቢው እንዲላክላቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው ጠይቀዋል፡፡ አቶ ደስታ ለ...
### Text: ደቡብ ክልል️በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት...
### Text: ሳውዲ አረቢያ የፀረሙስና ዘመቻዋን እንዳጠናቀቀች አስታወቀች። ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ በፀረሙስና ዘመቻው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር አሊአላሙዲንን ጨምሮ በመቶዎች ሚቆጠሩ የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባላት እና ቢሊየነር ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል። የባህር ሰላጤዋ ን...
### Text: 553 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ተመለሱአምስት መቶ 53 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ በሳኡዲ አረብያ ጂዛን ግዛት ኢዋ እና ሲጂንነዓም በተሰኙ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 280 ኢትዮጵያውያን ትናንት ከሌሊቱ በ8፡30 ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ኢትዮጵያዊያኑ ከ5 ዓመት እስከ 30 ዓመት ድረስ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጅዳ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄነራል ጽቤት በኩል የሳኡዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው በተደረሰው ስምምነት መሰ...
### Text: ፓስፖርት ለማውጣት የልደት ማስረጃ የሚጠየቁት እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 አመት ለሆናቸው ዜጎች ብቻ ነው ተባለ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜጎች ፓስፖርት ለማውጣትና ለማደስ ሲመጡ የሚያቀርቡት የነዋሪነት መታወቂያና የድጋፍ ደብዳቤ ህገወጥ አሰራር እንዲበራከት በማድረጉ ከዚህ በኋላ የልደት ሰርተፊኬትና መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ማለቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም የልደት የምስክር ወረቀት የትና እንዴት ማግኘት ይቻላል፣ የተወለድንበትን ቀንና አመተ ምህረት በትክክል...
### Text: ህገ ወጥ ቤቶቹ መፍረስ ጀምረዋል የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ አዉሮፕላን ማረፊያ አጠገብና አካባቢ የተገነቡ «ሕገወጥ» ያላቸዉን ቤቶች ማፍረስ ጀመረ። ቤቶቹን የሚያፈርሰዉ ግብረኃይል «ሥራ» እንዳይታወክ የከተማዋ አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስን እና ባካባቢዉ የሠፈረዉ የሐገር መከላከያ ሠራዊት ፀጥታ እያስከበሩ ነዉ። ይሁንና የቤቶቹን መፍረስ የሚቃወሙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቤቶቹን በሚያፈርሱት ላይ ድንጋይ በመወርወር እና ጎማ በማቃጠል እርምጃዉን ተቃዉመዉታል።አንዳንድ ተሽከርካሪ...
### Text: በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው 2ኛው የኢትዮ ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ምጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡ከጥቅምት 302013 ዓም ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አቶ ደመቀ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ ይህም በትግራይ ክልል የተፈጠረው ቀውስ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ...
### Text: የባይደን ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ሀገራት እነማን ናቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት0ጆ ባይደን0ዴሞክራሲን በተመለከተ በመጪው ታህሳስ ወር ሊያካሂዱ የኦንላይ ጉባኤ ያካሂዳሉ። ለዚሁ ጉባዔ የ110 ሃገራት መሪዎችን ጋብዘዋል።ጉባዔው በዋናነት ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነን የሚሉ እሳቤዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በፈረንጆቹ ታህሳስ 9 እና 10 2021 የሚካሄድ ነው፡፡በጉባዔው ሩሲያ እና ቻይና አልተጋበዙም፡፡ሩሲያ ሃገራትን ለመከፋፈል የሚደረግ ነው ስትል የባይደንን የጉባዔ ጥሪ ኮንናዋለች፡፡ ቻይና ...
### Text: ጋምቤላዩኒቨርሲቲ በጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን ለዞኑ ወጣቶችና ነዋሪዎች ስራ ለመፍጠር እንዲያግዘው የጋምቤላ ዩኒቨርስቲን ጠየቀ። የሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በትናትናው ዕለት በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን የሚገኘውን አልዌሮ ሰው ሰራሽ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ፕሮፌሰር አፈወርቅ በከፍተኛ አሳ ምርት የሚታወቀውን ግድብ የጎበኙት ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በመሆን ነበር፡፡ የአኙዋክ ዞን አስተዳዳሪ ለዩኒቨርስቲው የድጋፍ ጥያቄያቸውን ያቀ...
### Text: በጉምቢ ቦርደዴ ግጭት የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ ለ10 ሰዎች ሞትና ለበርካታ ዜጎች ጉዳት መንስኤ በሆነው በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ላይ የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ፡፡በቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር እና የሰዎች ህይወት ህልፈት ላይ የአመራሮች እጅ እንደነበረበት ተሰምቷል፡፡በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከወረዳው ሊቀመንበር ጀምሮ የተለያዩ አመራሮች፣ የቦርደዴ...
### Text: የምስራቅ ሀረርጌ ፖሊስ መምሪያ️በቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ላይ ለመገኘት የሚመጡ ምዕመናን እና ቱሪስቶችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡በመምሪያው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ሀላፊ ኮማደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለፁት ነገ የሚከበረውን የንግስ በዓል ለማክበር በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ቱሪስቶችና የሀይማኖት አባቶች ወደስፍራው ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በመሆኑም የእንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል...
### Text: በራስ አምባ ትቤት በኮቪድ19 የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸው ናሙና እየተወሰደ ነው በራስ አምባ ትምህርት ቤት ከኮቪድ 19 በሽታ የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸዉ ናሙና ከተማሪዎች እየተወሰደ መሆኑ አሀዱ ራድዮ 943 ዘገበ።በራስ አምባ ትምህርት ቤት በኮቪድ 19 ያለባቸዉ 4 ተማሪዎች በመገኘታቸዉ በየክፍሉ ምርመራ መደረግ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መመህር አቶ ስንታየዉ ገለታ ተናግረዋል፡፡አሁን ናሙና ከተወሰደላቸዉ 22 ተማሪዎች በተጨማሪ በሁለተኛዉ ዙር በነገዉ እለት ማክሰኞ ከ3 ክፍሎ...
### Text: የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል። ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።ፈተና እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ...
### Text: ነሃሴ 122012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 437 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 44 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 515 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።5 ከማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ1 ከህዳሴ ኤርፖርት 1 ሰው ከአሶሳ በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 698 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያ...
### Text: አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎችን ከሰኔ 32011 ዓም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወሮ ጽዮን ተክሉበሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች ተረጋግተው በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የተማሪዎችን ስነልቦና የሚያጠናክሩ ሥራ...
### Text: የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።መስከረም 72014 ዓም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትም...
### Text: በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ ክላስተር አደረጃጀትን ባለማጽድቅ ብቸኛ የሆነው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሐሙስ ነሐሴ 52014 እንደሚያካሂድ ተገልጿል።የአስቸኳይ ጉባኤውን መጠራት የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ እንዳረጋገጡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።ድረገፁ አነጋግሬያቸዋለሁ ያላቸው ሶስት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባላት በነገው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደተላለፈላቸው ገልጸዋል። የጉራጌ ዞን ምክ...
### Text: በሀዋሳ ከተማና አካባቢው ትናንት ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክለሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል ለፋና ብሮድካስት እንደተናገሩት በግጭቱ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ዛሬ ላይ ከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ይታይባታል ብለዋል።ግጭቱ ትናንት በታቦር ክፍለ ከተማ መንገድ በመዝጋት መጀመሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። እንዲ...
### Text: ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ በተባለ ቦታ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ጥቃቱ መፈጸሙን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው አጭር መረጃ አረጋግጧል። የአፋር እና የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ በምትገኘው ጉምቢ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች መካከል አንዲት እንስት እንደሚገኙበት እና ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን...
### Text: የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ምክር ቤት የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት እንዲፀድቅላቸው አቀረቡ።ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረቡት ሹመት መሰረት፡1 ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ2 ኢንጅነር ሰናይት ዳምጠው የቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ3 ወይዘሮ ነጂባ አክመል የፋይናስ ቢሮ ሃላፊ4 አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ5 አቶ አብዱልቃድር መሀመድ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ...
### Text: በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በሚፈቱበት አካሄድ ላይ ከተወካዮቻቸው ጋር ውይይት ሊደረግ መሆኑ ታውቋል።የክልሉ መንግስት የተሃድሶ ስልጠና ሃሳቡን ያቀረበው ከጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጉህዴን ታጣቂዎች ጋር ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2014 በይፋ ዕርቅ መፈጸሙን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።በጉሙዝ ባህል መሰረት የተከናወነው የዕርቅ ስነ ስርዓት የተካሄደው በካማሺ ዞን ካማሺ ከተማ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽና በካማሺ ወንዝ ዳ...
### Text: ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል️በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት 34 ሰዎች ለነገ ተቀጠሩ።በጎሃ አጽብሃ መዝገብ የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ለነገ የተቀጠረው።ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ አቅርቦት የነበረውን አዳምጦ ከቀረቡት 36 ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።16ቱ ተጠርጣሪዎች መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የፈቀደ...
### Text: አሳዛኝ ዜና️ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ወደ ምዕራብ በለሳ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓጓዝ የነበረ አይሱዚ የደረቅ ጭነት ማመላላሻ ተሸከርካሪ ተገልብጦ የ20 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ የመንገድ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር ውህብነህ አስናቀ እንደተናገሩት ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ አደጋውን ያደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 01254 አዲስ አበባ የሆነ የጭነት ተሸከርካሪ ነው፡፡የጭነት ተሸከርካሪው ከያዘው 25 ኩንታል ...
### Text: ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 316 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።ከሰላሳ አንዱ 31 መካከል 21 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 8 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 241 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በቫይረሱ መያ...
### Text: መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነው አቶ ደመቀ መኮንን የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ይደግፋል ሪታ ላራንጂንሃዛሬ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆኑት ሪታ ላራንጂንሃ ውይይት አካሂደው ነበር።በዚህም ወቅት አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን...
### Text: የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አደረጉ።ከቀናት በፊት ለሶማሊያው ፕሬዜዳንት ተመሳሳይ መልዕክት መላካቸው ይታወሳል።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህም ወቅት ከፕሬዜዳንት አልሲሲ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል ተብሏል።መልዕክቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ አህጉራ...
### Text: የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መረጠ።የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባውን በዛሬው እለት አጠናቋል።የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ስብሰባውንብ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችንና ምትክ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመምረጥ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።በዚህም መሰረት የኦዲፒ ማእከላዊ...
### Text: በጎንደር ከተማ የደረሰ እሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ በጎንደር ከተማ አዘዞ ቀበሌ 19 ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በ3 የእህል ወፍጮ ቤቶችና በአራት ጊዚያዊ የእህል መጋዘኖች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል።የከተማው ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር አበበ አለባቸው እንዳሉት ቃጠሎው የደረሰው 0በከተማው የአውቶብስ መናኸሪያ አጠገብ በሚገኙ ጊዚያዊ የገበያ ስፍራ አጠገብ ነው፡፡ምሽት አ...
### Text: ሀገርን አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች ላይ በሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተራድኦ ድርጅቶች ላይ እርምጃዎች ይወሰዳል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲየኢትዮጵያን ሉዕላዊነት፣ አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች እንዲሁም ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በሚንቀሰቀሱ አንዳንድ የተራድኦ ድርጅቶች ላይ በቅርቡ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስታወቀ።የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለፁት፣ የሀገሪቱን ህግና ...
### Text: ሁላችሁም የውጭ አገራት ጣልቃ እንዳትገቡ ኮሎኔል ሜጀር አማዱበአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ በተደጋጋሚ ተሰምቷል።አሁን ደግሞ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አውጀዋል።ወታደሮሹ ሕገመንግሥቱን መበተናቸውን ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ለጊዜው ሥራ ማቆማቸውን እና የሃገሪቱ ድንበሮች መዘጋታቸውን ይፋ አድርገዋል።ከረቡዕ ጀምሮ የኒጀር ፕሬዝደንት ሞሐመድ ባዙም በወታደሮች ቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተነግሯል።ተመድ እንዲሁም አሜሪካ ለፕሬዝደን...
### Text: ህወሃት️5ኛ ቀኑን የያዘው የህውሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬ ውሎው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬው ውሎው የማእከላዊ ኮሜቴ አባላት ምርጫ ያካሄደ ሲሆን የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥርም ከ45 ወደ 55 ከፍ እንዲል ወስኗል።በዚህም መሰረት 65 እጩዎች ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የ55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫተካሂዷል።ለማእከላዊ ኮሚቴ ከተመረጡት 55 ውስጥ 45ቱ ለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነት የሚቀርቡ ይሆናል።ለማእ...
### Text: የፈረሰውን በቅርስነት የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት ጥረት ይደረጋልየአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝምበአዲስ አበባ ትላንት የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት እንሚንቀሳቀስ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የሚገኘውና በቅርስነት የተመዘገበው መኖሪያ ቤቱ በትላንትናው ዕለት መፍረሱ ይታወቃል፡፡የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳዩን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ወደ ...
### Text: 19 ህዝብ አሸብሮ የዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰብከዩትዩብ ገንዘብ ለማግኘትና እውቅና ለማትረፍ ሲባል ብቻ ያልተፈጠሩ ነገሮችን እንደተፈጥሩ አስመስሎ፣ እንዲሁም ተመልካች ለማግኘት ሲባል የተጋነኑ ርእሶችን በመጠቀም ህዝቡን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሸብሩ አካላት አንድ ሊባሉ ይገባል። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የጤና ሚኒስቴር በየወቅቱ በቂ መረጃ በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ለህዝብ እያደረሱ ነው። የተጠርጣሪዎችን ናሙና የመረመሩ ይመስል እንዲሁም የጠለቀ...
### Text: የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት የተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።ከእነዚህ ውስጥም 21 ተመራቂዎች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል። እነዚህ ተመራቂዎችም ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመለከተው።የኢፌዴሪ ...
### Text: ትላንት ለሊት 6 ሰዓት ገደማ በሚዛን ማረሚያ ተቋማ መዝናኛ ክበብ የተነሳው እሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደረስ መቆጣጠር ተችሏል በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ማረሚያ ተቋም መዝናኛ ክበብ ላይ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ እሳት አደጋ በፀጥታ ሃይል እና በሚዛን አካባቢ ማኅበረሠብ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በማረሚያ ተቋሙ መዝናኛ ክበብ ላይ ሲሆን ከታራሚዎች መኖሪያ ጋር ግንኙነት እንደሌለውም ተገልጿል።ኮማንደር ዳዊት ጢሞቲዎስ የቤንች ሸኮ ዞን ሰላም እና ፀጥታ ...
### Text: የጆ ባይደን እና የአል ሲ ሲ የስልክ ውይይት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትናንት ሰኞ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ከሁለቱም ወገን የወጣ መግለጫ አመልክቷል።ሁለቱ መሪዎቹ በውይይታቸው ግብጽ ከ ኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ስለገባችበት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንስተው መወያየታቸውን ከፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አልሲሲ ከሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በ...
### Text: የሩሲያ እና የ ፍጣጫ ወዴት ያመራ ይሆን ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ሩስያ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋታቸው በአካባቢው ላይ ወታደራዊ ፍጥጫ ከምን ጊዜውም በላይ እንዲያይል አድርጓል።ሩስያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር በማንቀሳቀሷ ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ብሏል። ይህንንም የተሰኘው በጀርመንኛ ቋንቋ የሚታተመው መጽሄት ዘግቧል። አንድ የ ዲፕሎማት ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የድርጅቱ ተወርዋሪ...
### Text: በጎንደር ከተማ በሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ከተፈጠረ ግጭት በኃላ በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን ባለው ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶችም መጠቃታቸው ፣ ከዚህም አልፎ ንብረት መውደሙ ፣ የግለሰብ ቤቶች መጠቃታቸውን የጎንደር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠምቤት በበኩሉ በጎንደር ሙስሊሙን የማጥቃት፣ መስጂዶችን የመድፈር እና ንብረቶቹን የማውደም የተደራጀ ጥቃት እናወግዛለን ብሏል።ዛሬ የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ...
### Text: አላማጣ️በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ውይይት በአላማጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በስብሰባው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮንገብረሚካኤል እና ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ውይይቱ በወቅታዊ ጉዮች ላይና በአካባቢው ባለው የልማት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት እንዳደረገም ተገልጿል።በውይይቶቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ለመስጠት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ረዳዒ ኃለፎምን ጨምሮ ሌሎች ...
### Text: አሳዛኝ ዜና️ሰባ ገደማ ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር የጀልባመገልበጥ አደጋ ሞቱ ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ እና የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሞቱ። ከሟቾቹ ውስጥ ስድሳዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተነሱ ነበሩ ተብሏል።ሰባ ገደማ ወጣቶች ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የመገልበጥ አደጋ የደረሰባት ቅዳሜ መጋቢት 28 ለሊት መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል። ከጀ...
### Text: ሪፖርት በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣ ማሰቃየት፣ ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣ በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ በማይካድራ ሳምረ በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃ...
### Text: ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስረኞች ማቆያ እንዲገቡ የተደረጉት ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።የሲዳማ ክልል መንግስት ምቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ 3 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ማቶ ማሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ያሏቸውን ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣ አቶ አበራ አሬራ አቶ ተሰማ ደንጉሼ ያለመከሰስ መብ...
### Text: መስከረም 22013 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 114 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በኮቪድ19 የተያዘ ሰው አልተገኘም። በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 51 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 682 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 80 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1408 የላብራቶሪ ምርመራ ተደር...
### Text: የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። 62 50 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።በዚህም መሠረት አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 50 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል 80 ያገኙ ተፈታኞች ብቻ...
### Text: ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ 1 ነጥብ 75 ግራም የጆሮ ጌጥ ወርቅ የዋጠው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ወርቅ ይውጣል። ነገሩ የተከሰተው ጳጉሜ 03 ቀን 2011 ዓም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡ ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤ...
### Text: አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው አቁም ማለት አልፈልግም ነው መሸሽ ማለት አልፈልግም ነው እምቢ ማለት አልፈልግም ነው መግፋትመገፍተር ማለት አልፈልግም ነው ዝግጁ አይደለሁም ማለት አልፈልግም ነው ተወኝ ማለት አልፈልግም ነው ዞር በል ማለት አልፈልግም ነው መጮህ ማለት አልፈልግም ነው እረፍ ማለት አልፈልግም ነው ማልቀስ ማለት አልፈልግም ነውየሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት ...
### Text: ለስድስት ወራት የተዘጋው በመተማ ጋላባት በኩል ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ነገ ክፍት ይሆናል ተብሏል።ዛሬ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምዕራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ተወያይተዋል፡፡ይህን በተመለከተ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ሐምሌ17 ቀን 2013 ዓም የመተማጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነ...
### Text: ከወጣት አምባሳደር ፕሮግራም ፀግሽ እንዴት ነክ ባሳልፍነው ሳምንት በደቡብ ክልል ከተሞች በተነሳው ግጭት ብዙ ወጣት ወገኖቻችን አልቀዋል ይህም በጣም ያሳዝናል፡፡ በዚህ ጉዳይ በማህበራዊ ገጾች ላይ በጣም ብዙ ምስሎች እና ቪድዮዎች የተለቀቁ ሲሆን፣ ወጣቱ በስሜታዊነት የተለያዩ የብሔር ስሞችን በመጥቀስ ስድብ እና መሰል ፅሁፎችን በማህበራዊ ገጾች ላይ እየተጠቀመ አይቻለሁኝ፡፡ይህ ተግባር እርስ በርስ አለመተማመንን፣ ቂምና ቁርሾን የሚያመጣ ሲሆን፣ በተቀረው አለም ያለንን ስምም የሚያጎድፍ ነው...
### Text: የኢቦላ ወረርሽኝ️በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና አሰከፊ ነው ሲል የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል።ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል።ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ክትባት ተሰጥቷል።ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የጤና ባለ...
### Text: የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር 14 እጩ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረጉየሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ 14 የካቢኔ እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።በእጩ ካቢኔ አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሹመት ቀርበዋል የዓለም ባንክ0የቀድሞው0የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ደግሞ ለገንዘብ ሚኒስትርነት ቀርበዋል።አስማ አብደላህ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እጩ ሲሆኑ ኢብራሂም ኤልባዳዊ ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትርነቱን እንዲመሩ በነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ለሹመት ተጠቁመዋል።የገንዘ...
### Text: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስራ አመራር ቦርድ አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው በአምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቦርድ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የመስክ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ በጉብኝቱ ወቅት አምባሰደር ግርማ እንደተናገሩት ጉብኝቱ ፕሮጀክቱን ከሰነድ ሪፖርት ባለፈ በአካል የማየት እና የመገምገም ዓላማ አለው።ጉብኝቱ ከፕሮጀክቱ የስራ ተቋራጮች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በመወያየት ያጋጠሙ ችግሮችና ደካማ አፈፃፀ...
### Text: አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራየኤርትራ ልዑክ ጥምቀትን በጎንደር እየታደመ ይገኛል። በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ የተመራ የኤርትራ ልዑክ ዛሬ ጠዋት ነው የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር የገባው። የከተማዋ ነዋሪዎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከአቀባበል ጀምሮ ላሳዩት አክብሮት አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል። አምባሳደሩ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተብሎ ይጠራ በነበረው በዛሬው ፋሲለደስ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤ...
### Text: ሱዳን ሱዳን ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን የሀገራችንን ዜጎች እያፈሰች እያሰረችና እየቀጣች ነው።ጎረቤት ሀገር ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን ዜጎቻችንን እያፈሰች እያሰረች ሲሆን በዛው ያሉ ዜጎቻችን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እየወቀሱ ይገኛሉ።ዜጎቻችን ከፍተኛ ቅጣት እየተጣለባቸው እስከ ድብደብዳ የደረሰ እንግልትም እየደረሰባቸው ኤምባሲው ዝምታን እየመረጠ ነው ሲሉ ተችተዋል።ኤምባሲው በበኩሉ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፓስፖርት የሌላቸው በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን ፓስፖርት እንዲ...
### Text: መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል። 200 0000 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ0 ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ዶር 0 በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ0 እንደገለጹት0መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ0 ወር ለሁሉም0ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች0 በአንድ ጊዜ0ይሰጣል።የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ0 ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ0የመውጫ ...
### Text: ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ የዛኔው ለጋ ህፃን የአሁኑ ታዳጊ መሀመድ ከዛሬ 12 አመት በፊት የ4 አመት ጨቅላ ህፃን ሳለ ነበር አፍንጫው ላይ የወጣችን አነስተኛ ስጋ ለማስነሳት ቤተሰቡ ጋር በሳኡዲ አረቢያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የገባው በወቅቱም እናቱ በገባበት የህክምና ክፍል አጠገብ ሁና የልጇን መውጣት ብትጠብቅም ሳይመጣ ቀረባት ከሰአታት ቡሃላም ፈፅሞ ያልጠበቀችው ያልገመተችው ዱብ እዳ ተነገራት ።ልጇ መሀመድ በጣም ደክሞ ህይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን ሰማች እንዴ በምን ምክንያት ልጄ እኮ ...
### Text: ለጋሾች ርዳታ ለማድረስ በእግር መጓዝ ጀምረዋል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽቤት ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።በአፋር በኩል በመጋሌ፣ ኢረብቲ፣ በራህሌ፣ ዳሎል እና አባላ ግጭት መኖሩን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በኩል፣ በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን ሪፖርት አድርጓል።በተቀረው የአማራ ክልል ሁኔታው 200200የተረጋጋ እና ለሰብአ...
### Text: የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 23 የመወያያ አጀንዳዎችን አጽድቆ በመወያየት ልዩልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ጀምሯል።ዓመታዊው የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓም በጸሎት ከተጀመረ በኋላ በትላንትናው ዕለት በጠዋቱ መርሐ ግብር የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ መልዕክት አዳምጧል። በመቀጠልም ሰባት አባቶችን የያዘ የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚ...
### Text: ስፖኪዮ የተሰረቀባችሁ ማስረጃ በማቅረብ ንብረታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን አስታውቋቃ።ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛልም ብሏል።ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አሜሪካን ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው በላስቲክ ...
### Text: ቤንሻንጉል ጉምዝ️ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ የገጠር መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረ ግለሰብ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበረው አቶ መልካሙ ታደሰ ላይ ነው።ግለሰቡ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ መሳሪያዎች ግዢ ለመፈፀም በወጣ ጨረታ የግዢ ስርዓቱን ባለመከተል ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን...
### Text: ምዕራብ ጉጂ ዞን️በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ማስተማር ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ 0አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል። በዞኑ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል። በአባገዳዎች ሰብሳቢነት አስተዳደሩ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ አባላት ጋር በመወያየት በአሁኑ ...
### Text: ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የሰው ኃይል ይፈልጋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ነው።ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ...
### Text: ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ25 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ በ25 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የጽህፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር አንዳርጌ በላይ እንደገለፁት አደጋው የተከሰተው ዛሬ ጠዋት 60 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 00830 አውቶብስ ኤፍራታና...
### Text: የአዲስ አበባና ዙሩያዋ ሰላም እና ፀጥታ ካለፈው ሳምንት ወዲህ አጠያያቂ ሆኖ ቀጥሏል ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በለቡ፣ ጀሞ፣ አስኮ፣ በአቃቂ ክከተማ የተለያዩ አካባዎች፣ ኮየ ፈጬ እና በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተደራጁ ወጣቶች ምክንያት ሰላም ደፍርሷል ህብረተሰቡም ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡የተደራጁ ወጣቶቹ ከየት መጡ ሳይባል መንገድ ይዘጋሉ፣ የጥላቻ ንግግሮችን በአደባባይ ያስተላልፋሉ፣ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዜጎችን ያስፈራራሉ ንብረትም ያወደሙ እንዳልጠፉ ለማወቅ ችለናል፡...
### Text: ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ወንድማዊ ትስስራችሁን አጥብቃችሁ ተረጋግታችሁ የትምህርታችሁን ጊዜ በአግባቡ እንድትጠቀሙ ቤተሰባዊ ምክራችንን እንለግሳለን ጅማ ዩኒቨርሲቲመላዉ የጅማ የኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተዉ ግጭት ህይወታቸዉን ላጡና የአካል እና መንፈስ ጉዳት ለደረሰበቸዉ ተማሪዎች የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ በእነዚህ በምንሳሳላቸዉ ልጆቻችን ላይ የደረሰዉ ጉዳት በዬትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለዉና ሰብአዊነትን ያልተላበሰ በመሆኑ...
### Text: የሚዲያዎቹ ተፅእኖከሰሞኑን ቢቢሲ ትግርኛ፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎክ እና አውሎ ሚዲያ በነጀነራል ሰዓረ ጉዳይ ባለቤታቸውን ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁን አነጋግረው ያለውን ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው አድርገዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ስለተፈጠረው ሁኔታ፣ ስለ ፍርድ ሂደቱ ፣ የጀነራል ሰዓረ ቤተሰቦች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ በግልፅ ሳያውቅ ከአንድ ዓመት በላይ ተቆጥሯል።ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁ ትላትን ምሽት በ በተሰራጨ ልዩ ዝግጅት ላይ ስለጉዳዩ ልክ እንደሌላው ሰው በፌስቡክ እና...
### Text: በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ቀይ መስቀልየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የምዕራብ ወለጋ ዞን ሀሩ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽቤት ንብረት የሆነ ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ 0501939 አምቡላንስ ተሽከርካሪ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በሀሩ ወረዳ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በቆመበት በታጣቂ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡ ማኅበሩ...
### Text: በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ ተጋልጧል ጃን አሞራ ወረዳ በሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሰዎች እና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ። በሰሜን ጎንደር ዞን በምትገኘው ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ 13 ቀበሌዎች በክረምት ወራት ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ መጋለጣቸውን የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ገልፀዋል ። አስተዳዳሪው አክለውም በድርቁ ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች ፣6500...
### Text: ዶክተር አብይ አህመድ ማናቸው ዶክተር አብይ አህመድ በአጋሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል። በግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ እና በሊደርሺፕ ተቋም ደግሞየሥራ አመራር ሳይንስ አጥንተዋል። እንዲሁም አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ በንግድ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ደህንነት ጥናት ፒኤችዲ አላቸው። በመጀመሪያ 40ዎቹ የሚገኙት ዶክተር አብይ ኦህዴድን የተ...
### Text: የእሳት አደጋአዲስ አበባ️በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ሶስት ቦታዎች የእሳትአደጋ መከሰቱን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ገለጸ፡፡የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ቁስቋም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ ንብረትነቱ የንግድ ባንክ በሆነ የቤት እቃዎች መጋዘን ላይ በ...
### Text: የኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 406 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 3 ከመተከል ዞን ጉባ ወረዳ 2 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ 1 ከአሶሳ ህዳሴ ኤርፖት በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 587 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል የሁለት ሰዎችም ህይወት አልፏል። አጠቃላይ በሀረሪ 432 በቫይረሱ የተያዙ 14 ሞት 80 ያገገሙ በትግራይ ክ...
### Text: ጥንቃቄ በድሬደዋ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን ተከትሎ የከተማው ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ከፍተኛ ደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአእምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።1 ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መ...
### Text: ሰላም ሚኒስቴር የአገር ግንባታ መሠረታዊያን በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ትላንት በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዶ ነበር።በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደኣ፣ መሰል የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው ግጭትና አለመግባባት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።በኢትዮጵያ ብዙ የሚያለያዩ ጉዳዮች ቢኖሩም ብዙ የጋራ ትስስር የሚፈጥሩ ነገሮች እንዳሉ፣ ይ...
### Text: 2022 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛዉ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።እስካሁን የገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች 0ፍሬድሪክ ሻቫ ዝምባብዌ ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ ሌዡን ቤላ ቤላ ካሜሩን ማህማት ዜኑ ሸሪፍ ቻድ ካንዲያ ካሚስኮ ካማራ ኮትዲቯር አብዲሳድ ሙሴ አሊ ሶማሊያ ዢያን ክላውዴ ጋኮሶ የሪፐብሊክ ኮንጎ ሀሱሚ ማሹዱ ኒጀር ምክትል ጠሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር...
### Text: መቀለ️ በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን0የካቲት 11 በዓል በጋራ አክብረዋል፡፡0በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡0በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1993 ዓም ህወሓት ካጋጠመው ክፍፍል በኋላ ነባር የሚባሉት የድርጅቱ አመራሮች ፖርቲው ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ መድረክ ተገናኝተው ትግል የጀመሩበት 44ኛውን ዓመት የካቲት 11 አክብ...
### Text: ዳኞች በክረምት ወራት በእረፍት ሰአታቸው ከአመቱ የተጠራቀሙ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንደጨረሱ ተነገረ፡፡ የተሻሻለው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኞች ስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብም ተመርቋል፡፡ዳኞች ለበርካታ አመታት መፍትሄ ያልሰጡባቸውን ውዝፍ የክስ መዝገቦች በእረፍት ሰአታቸው እልባት ለማሰጠት የመግባቢያ ሰነድ በተፈረመበት ወቅት የበጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ እንዳሉት ዳኞች በመጪው የክረምት ...
### Text: በህገወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ በህገወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወሮ ፈትለወርቅ ገእግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በአገልግሎትና በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በአቅርቦት ችግር ሳይሆን የህገወጥ ደላሎች ጣላቃ ግብነት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ የዋጋ ንረቱ በተለይም በደሃው ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታ...
### Text: የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እየተጠገኑ ነው።ከገረገራ እስከ ጋሸና ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ይገኛል።ከህዳር 23 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በተካሄደ የፍተሻ ሥራ ሠላሳ አራት በሚሆኑ በታወሮች መካከል በሚገኙ ቦታዎች ላይ 50 የመስመሮች መበጣጠስ፣ 7 የድምፅና ዳታ ማስተላለፊያ የኦፕቲካል ፋይበር መቆረጥ እና 13 ቦታዎች ላይ መስመር ሳይበጠስ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ሥ...
### Text: መንግስትቶሎ ወደ ስራ ያስገባን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተርብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለቤቶች አስተዳደሩ ያወጣውን የአፈፃፀም መመሪያ ማስተካከያ አድርጎ ቶሎ ወደ ስራ እንዲያስገባቸው ጠየቁ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት የማሽከርከር ስልጣን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ላይ እያወያያቸው ነው፡፡መመሪያው ሞተር ብስክሌቶች የፍጥነት መቆጣጠሪያ ማስገጠም እንዳለባቸው እንዲሁም የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰሌዳቸውን ወደ 3 ቁጥር መለወጥ እንደሚኖርባቸው፣ በከተማዋ ...
### Text: የአፍጋኒስታን ሴቶች ተቋውሞ ታሊባን በአፍጋኒስታን ካቡል ከተማ ስለመብታቸው ለመጠየቅ ተቃውሞ የወጡ ሴቶች መበተነ ታውቋል።ሰልኞቹ ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ላይ እያሉ ታሊባን አስለቃሽ ጭስና አይን የሚያቃጥል ሌላ ፈሳሽ ጭምር በመጠቀም ሰልፉን ለመበተን ጥረት አድርጓል።አንዳንድ የአፍጋኒስታን ሚዲያዎች እንዳሉት ከሆነ ታሊባን ተቃውሞውን ሙሉ በሙሉ መበተን አቅቶት እንደነበርና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እንደነበር ዘግበዋል።ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች የካቡል ሴቶች ተቃውሟቸውን አደባባ...
### Text: ድሬ በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ። ለጊዜው0 ምክንያቱ ባልታወቀ0 ሁኔታ0 በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት 46 ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ ነው፡፡ከቀኑ 5 ሰአ...
### Text: የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ1 የሶሻል ሳይንስ ሴቶች መግቢያ ውጤት 164 እና በላይ2 የሶሻል ሳይንስ ወንዶች መውጤት ውጤት 174 እና በላይ3 የናቹራል ሳይንስ ወንዶች መግቢያ ውጤት 176 እና በላይ4 የናቹራል ሳይንስ ሴቶሽ መግቢያ ውጤት 16...
### Text: በኦሮሚያ ክልል አባ ቶርቤ የሚባልና ጽሑፍ ያለው ወረቀት እየበተነ 0አስጠንቅቆ 0ሲያበቃ ቀጠሮ ሰጥቶ የሚገድል የተባለ አካል የክልሉን ሰላም እያወከ መሆኑን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።አቶ ጌታቸው ባልቻ ለዶቼ ቬለ የተናገሩትትናንት በአምቦ ከተማ ለመንግሥት ድጋፍ የወጡ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማስቆም 0ያሰበ ግን ያልተሳካ ያሉት የቦንብ ጥቃት ተሰንዝሮ 29 ሰዎች ተጎድተዋል። ከተጎጂዎቹ 0አንዱ ብቻ አሁንም በህክምና ላይ እንደሚገኝ ቀሪዎቹ ግን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። በጉዳዩ...
### Text: የካንሰር ቀን️በኢትዮጵያ ያለው የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ፡፡ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሀ አገራት ላይ ይበረታል ተብሏል፡፡ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ...
### Text: የሰላም ዋጋ በሞቃዲሾ የሱማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ስታዲየም ለዓመታት ስፖርታዊየእግር ኳስ ጨዋታዎችን አያስተናግድም ነበር።በሀገሪቱ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ፣ የሽብር ጥቃት የሱማሊያ የስፖርት እንቅስቃሴ ተደክሞ ነበር ታድክሞ ብቻ ሳይሆን ሞቶም ጭምር ነበር።ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ሀገሪቱ በአንፃራዊነት እየተረጋጋች ፣ ሰላሟም እየተመለሰ ከእርስ በእስር ጦርነቱ እያገገመች ስትመጣ የስፖርት እንቅስቃሴው መነቃቃት ጀምሯል።የአሚሶም ወታደሮች መቀመጫ የነበረው የሞቃዲሾ ስታዲየም ...
### Text: አሶሳ መናናቅ አያዋጣም ልክ እንደ በቆሎው ምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድመናናቅ መጠላላት ትክክል የማይሆነው የሚናቅ ሰው የሚናቅ ማህበረሰብ ስለሌለም ጭምር ነው፡፡አሶሳ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ድንበር ጠብቋል፡፡ ድንበሩ ክፍት ከሆነ ወለጋ የለም ማለት ነው፡፡ሸዋ የለም ማለት ነው፡፡ መናቅ አይቻልም፡፡ኦሮምያ ተማምኖ የሚተኛው ወንድሞቼ ቤኒሻንጉል ህዝቦች ድንበር ይጠብቃሉ ብሎ ነው፡፡ቤኒሻንጉልም ወደመሃል ሃገር ሲያስብ ወንድሞቼ አሉ ብሎ ማሰብ አለበት፡፡በቆሎ በመጠንዋ ከጤፍ ከፍ ትላ...
### Text: ለፋሲል ግቢ የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ አመራር በሙሉ ጉዳዩ ከቤንሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግ ስለመጠየቅ ይመለከታልከላይ በርእሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በያዝነው አመት ከቤንሻንጉልጉሙዝ ክልል የአማራ ብሄር ተወላጆችን ማእከል ባደረገ መልኩ ዜጎች ለዘመናት ሀብታቸውን ካካበቱበት ቀዬአቸው ተፈናቅለው በባህርዳር ቅዱስጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን በጊዜያዊነት ተጠለው ይገኛሉ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የግቢያችን መምህራኖች በቅርቡ ገንዘብ አሰባስበው ከ5...
### Text: የፅዳት ዘመቻበኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ በሁሉም ከተሞች፣ መንገዶች እና ሰፈሮች የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትናትናው እለት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ሚያዚያ 6 ቀን 2011 በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡ይህ የፅዳት ዘመቻ በመላ ሀገሪቱ እሁድ ጠዋት 1፡ 30 ጀምሮ እስከ ሶስት እንደሚካሄደ የወጣው መርሃ ግብ ያመለክታል፡፡የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ባስተላለፈው ጥሪ የምናጸዳው በክብርና በንጹሕ አከባቢ መኖር መብታችን እንደሆነ ስለ...
### Text: 37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ️ባለፈው ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተ...
### Text: ለከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተጋነነ ዋጋ የሚገዛው ሞባይልና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ህገወጥ ነው ለአንድ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ እስከ መቶ ሺህ ብር ግዢ ተፈጽሟልለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተጋነነ ዋጋ ተንቀሳቃሽ ስልክና ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚገዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የግዥን መመሪያና ህግ እየጣሱ በመሆኑ ህገ ወጥ መሆናቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ለአንድ ባለስልጣን አንድ ስልክ እስከ መቶ ሺ ብር ግዥ መፈጸሙንም ገልጿል።የኤጀንሲው ዋና...
### Text: ኢህአዴግ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባውን በሚቀጥለው ሳምንት ያካሄዳል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሶስት ብሄራዊ ድርጅቶችን የግምገማ ሪፖርትን በዝርዝር መመልከቱን ገለፀ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በታህሳስ ወር ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች አፈፃፀም ላይ በዝርዝር የሚያደርገውን ግምገማ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢቢሲ እንዳስታወቁት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በታህሣስ ባካሄደው የ17 ቀናት ስብሰባ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ብሄራዊ...
### Text: አዲስ አበባ️በአዲስ አበባ በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ ዶላር በነሐሴ ወር 2010 ዓም መያዙን የከተማይቱ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች ከቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን በየቀኑ ማታ ማታ በካርቶን የታሸጉ ብሮች ያወጡ እንደነበር ከአስራ አምስት ቀን በላይ ከፈጀ ጥብቅ ክትትል በኋላ ፖሊስ ደርሶበታል፡፡ነሀሴ 28 ቀን 2010 ዓም ምሽት ላይ መነሻዋን ከቦሌ ሻላ ያደረገች ፕራዶ...
### Text: ወንጀል ነክ መረጃ️የስራ ባልደረባውን የገደለው የፖሊስ አባል በጽኑእስራት ተቀጣ፡፡ በጋምቤላ ክልል ልዩ ቦታው ደንቦስኮ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 3፡00 በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ የስራ ባልደረባውን የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ተከሳሹ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሲሆን ከሌሎች አስራ ሁለት አባላት ጋር ለግዳጂ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክ...
### Text: ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በድርጊቱ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸውበባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው። የጀነራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እየተነበበላቸው ነው።ተጠርጣሪ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍን...
### Text: በአሜሪካ ኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የ...
### Text: ችሎትበፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ0 ከአራተኛ እስከ 14ኛ0 የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድና አቶ በቀለ ገርባ ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አ...
### Text: ፍርድ ቤቱ ሀያት ቲቺንግ ሆስፒታልን በነፃ አሰናበተ የሸማቶች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሀያት ቲቺንግ ሆስፒታል የቀድሞ ባለቤቶች የአክሲዮን ድርሻቸውን ለሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ድንቁ በያሳ እና ወላጅ እናታቸው ዳንሳ ጉርሙ መሸጣቸው ሕገወጥ ውሕደት ነው በሚል ከቀረበባቸው ክስ ኅዳር 282011 በነፃ አሰናበታቸው።ግንቦት 262011 የተመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው ዳንሳ ጉርሙ ከፍተኛውን አክሲዮን በመያዝ ድርጅቱን የገዙ ሲሆን ይህ ውል እንደ...